የአባይ ውሃ ጦርነት ታምቡር ከምድረ ምስር እና አንደምታው

ዘሪሁን አበበ ይግዛው

Nile new diversionየሰሞኑን የአባይ ውሃ ፖለቲካን ልብ ብሎ ላተዋለ ግራ መጋባቱ አይቀርም፡፡ የግብጹ ፕሬዝዳንት ሀገራዊ የውይይት መድረክ ብለው በሰየሙት እና የኢትዮጵያን የታላቁ ህዳን ግድብ አጀንዳ አድርገው በጠሩት ጉባኤ ላይ እጅግ ሀገራቸውን ያዋረደ እና ያሰደበ ተግባርን ፈጥመዋል ግብጻውያን ፖለቲከኞች፡፡ አንዳንድ ፖለቲከኞች በተለይም አክራሪዎቹ ኢትዮጵያን በውሸት ወሬ ፍርሃት እንልቅባት ከማለት ጀምሮ እስከ ታጣቂ ኃይሎችን አንርዳ እስከማለት እንዲሁም ወታደራዊ ኃይላችንን እና የስለላ መረባችንን ተጠቅመን ግድቡን እናውድምም ያሉ አልጠፉም፡፡ ይህ ያሉት ነገር በሙሉ ፖለቲከኞቹ የሚመኙት ነገር እንደሆነ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ ባይናገሩትም የዕውነት ምን እንደሚያስቡ ስለሚታወቅ አዲሰ ነገር የለውም፡፡ አዲስ ነገር የሆነው ይህ ውይይት በቀጥታ ለዓለም ህዝብ በትዕይንተ-መስኮት (ቴሌቪዥን) መተላለፉ ነው፡፡ ይህም በርግጥ ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ ለረጅም ጊዜ ኢትዮጵያ ግብጽን እንዲህ ሸማቂዎችን እያስታጠቀች ነወ ብላ ስትከስ ግብጽ በበኩሏ እኔ በፍጹም አላደረግሁም ሀራም ነው እያለች ድስኩሯን ታሰማ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ይሄው የሆነው ሆነ እና ዓለመ ጉዱን ገለጸው፡፡ ይህ ውይይት የፖለቲካ ፓረቲዎቹ እንጅ የግብጽ መንግስት ሀሳብ አይደለም ሊባ ይችላል፡፡ ይባል፡፡ ነገር ግን ፕሬዝዳቱ ሳያውቁ በስህተት በቀጥታ ስርጭት አየር ላይ ዋለ ማለት ዘበት ነው፡፡ ይሁን ግድ የለም ምኞታቸውን ነው የገለጹት፡፡ ምኞት ደግሞ አይከለከልም፡፡ ግን አንድምታው ምንድን ነው፡፡

Guba GERD

ሀ. ዛቻ የድርድር አካል?

ግብጻውያኑ አንዳንዴ ያሳዝናሉ ያስገርማሉም፡፡ አባይን መያዝ እና ምንም ሳይነካ ሀገራቸው እንዲገባ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሲሆንም ሌላው ወንዙን የሚጋራ ህዝብ ምንም መብታ ያላቸው አይመስሉም፡፡ እነሱው ማ ውሃ እንደሚጠቀም እና እንደማይጠቅም ፈቃጅ እና ከልካይ መሆንን ይሻሉ፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል…? ምልሱ ግልጽ ነው፡፡ ሊሆን አይችልም የሚል፡፡ ሆኖም ግን ይ በትዕይንተ-መስኮት የተላለፈ ወሬ እና ድራማ አንዳች ነገር በውስጡ አለው፡፡ ኢትዮጵያን በተመለከተ፡፡ ይህም አንዲህ ማጓራትን እና ዛቻን የድርድር አካል ማድረግ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ጦርነትን ለማስወገድ ብላ አባይን መገደቧን የምታቆም እንዳሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ አንዳችም ስንዝር ወደ ኋላ እንደማትልም ተገንዝበዋል፡፡ በ90 ሚሊዮን ልብ ውስጥ ያለን ነገር እንዴት ማስወገድ ይቻላል? አይሆንም፡፡ ነገር ግን በዚህ ግርግራቸው ውስጥ ግብጻውያ ደጋግመው የተናገሯቸው እና ከአፋቸው ያልነጠሏቸው ቃላቶች አሉ፡፡ “ይህ ግድብ የውሃ ኮታችንን መቀነስ የለበትም፡፡ ይህ ግድብ የውሃ ዋስትናችንን መንካት የለበትም፡፡” የሚሉ፡፡ የትኛው የውሃ ዋትና ተብለው ሲጠየቁ መልሱ ወደ 1959 ከሱዳን ጋር የተደረገ የውሃ ክፍፍል ስምምነት ይወስደናል፡፡ ነገር ይህ ስምምነት ለኢትዮጵያ ምኗ ነው? ምኗም አይደለም፡፡

በዓለምአቀፍ የስምምነት መርሆ መሰረት አንድ ሀገር በሀገራት መካከል በተደረግ ስምምነት ሊቀየድ ወይም ተገዥ ሊሆን የሚችለው አንድም የስምምነቱ አካል ሆኖ ተደራድሮ እና አምኖበት ሲፈርም እና ሲያጸድቅ ነው፡፡ ሁለትም ስምምነቱ በሌሎች ድርድር ሂደት ከተፈረመ እና ከጸደቀ በኋላ አመልክቶ ከገባ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይን ሁሉ አላደረገችም፡፡ ስምምነቱ ሲደረግ የጋበዛት የለ፡፡ እሷም አላመለከተችም፡፡ ስለዚህ አያገባትም፡፡ ይልቅ አንባን አንድ ነገር ላስታውስ፡፡ ይህ ስምምነት ለኢትዮጵያ ታላቅ ብሔራዊ ስድብ ነው፡፡ የአባይን ከሰማንያ ስድስት በመቶ በላይ የምታመነጭ ሀገር የሥምምነቱ አካል ሳትሆን የተፈራረሙት ሀገራት ስምምነቱን “የአባይን ውሃ ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም በተባበሩት የአርብ ሪፐብሊክ (ግብጽ) እና በሱዳን ሪፐብሊክ መካከል የተደረ ስምምነት” ሲል ይጀምራል፡፡ ከዚህ በላይ ስድብ ከየት ይመጣል? ሁለተኛው ስድብ ውስጥውስጡን እንተው እና ዋናውን ጉዳይ ለማንሳት ይህ ስምምነት ተብየ የአባይ አጠቃላይ ዓመታዊ ፍሰት ለግብጽ 55.5 ቢሊዩን ኩቢክ ሜትር፣ ለሱዳ 18.5 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር እንዲሁም ሰሐራ በረሐ ላይ በተሰራው የአስዋ ግድብ ምክንያት ለትነት ከ10 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ያከፋፍላል፡፡ እንግዲህ ግብጽ ይህን ነው የውሃ ደህንነቴ/ዋስትናዬ ወይም የውሃ ኮታዮ የምትለው፡፡ የሰሞኑ ጩኸትም ይህን ነገር ተቀበሉን ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ከላይኛው ተፋሰስ ሀገራት አንጻር የሚሆን አይደለም፡፡ በአባይ የትብብር ሰምምነት ማዕቀፍ ውስጥ ያለ ነገር ስለሆነ ከግድቡ ጋር የሚያይዘው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ግብጽ የአባይ አውራ የሆነችውን ባለ ብዙ ውሃዋ ሀገር ኢትዮጵያን ግድቡን ስሪ 1959 ስምምነትን በጓዳ ተቀበይ አይነት ጥሪ መሆኑ ነው፡፡ ግን ይሆናል ወይ? መልሱ አንድ ነው አይሆንም፡፡ ታዲያ ግብጻውያን እንዲህ ለምን የጦርነት ታምቡር ደለቁ?

ለ. ፖለቲካን ከውስጥ ወደ ውጭ

ወደ ዝርዝሩ አንግባበት እንጅ በአሁኑ ስዓት የቀድሞውን መሪ ሞሀመድ ሆስኒ ሙባርክን ከስልጣን ካወገደች በኋላ ግብጽ በሁት እግሯ የመቆም ነገር አልሆንላት እያለ ተቸግራለች፡፡ የፕሬዝዳቱ እንደ ፈርኦን ልሆን ብሎ ወዲያ ወዲህ ማለት፣ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በተያያዘ፣ ከሊበራሎች ጋር በተያየዘ እንዲሁም እጅግ በጣም ከሚያከሩት ከሳላፊስቶች ጋር በተያያዘ፣ የሐይማኖትን ጉዳይ ተከትሎ በክርስቲያች ላይ እየደረሰ ያለው ችግር እንዲሁም የህገ-መንግስቱን በግርግር እና በሁካታ መጽደቅ ተከትሎ ያለው መከፋፈል በጥቅሉ የሞርሲን ወንበር እየነቀነቀው ይገኛል፡፡ እናም ትንሽ የህዝባቸውን ሀሳ በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስብ ፖለቲካ ፓርቲዎቹን ከመረበሽ የሚያበርድ ትኩስ ዳቦ ሲፈለግ ይሄው ግንቦት ፍጻሜው ሰኔ መጨረሻው ሆኖ አገኙት፡፡ ስለሆነም አንደኛ የኢትዮጵያ አባይን ግድቡን በሚገባ ያለመስተጓጎል ለመስራ እንዲያስችል የወንዙን አቅጣጫ በተወሰኑ ሜትሮች የማስቀየሷ ዜና አባይ ወደ ሌላ አቅጣጫ ያስተላለፈች እና ያፈሰሰች በማስመሰል የተሰራጨው ዘገባ ጥሩ ምቹ ሁኔታን ፈጠረላቸው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የህዳሴ ግድቡን አጠቃላይ ሁኔታ በተለይ በግርጌ ተፋሰስ ሀገራ የሞያደርሰው የጎላ ጉዳ እንዳለ እና እንደሌለ የተሰየመው የባለሙያዎች ቡድን የመጨረሻ ሪርፖርቱን ይፋ ማድረጉ እና ተጨማሪ ጥቅሞች ካሉ ድንገት ያልታዩ ጉዳቶችም ካሉ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥናት ቢደረግ ብሎ ያቀረበው አስተያየት ለፕሬዝዳት ሞርሲ እና መንግስታቸው ሰርግ እና ምላሽ ሆነ፡፡ ቢሆን መልካ ነው የተባለውን ነገር ግብጾች የኢትዮጵያ ጥናት የቆየ ነው ይቀረዋል ወዘተ ወደሚል አተካራ ገቡ፡፡ ነገር ግን የባላሙያዎች ቡድኑ ሪፖርት በግርግ ተፋሰስ ሀገራ ላይ የሚያመጣው የጎላ ጉዳት የለም የሚለው ለግብጽ ብቻ አልተነበባትም፡፡ ስለሆነም አቅጣጫ ማስቀየሱን እና የሀገር ውስጥ ፖለቲካውን ማተንፈሱ ለሞርሲ በግማሽም የሰራ መሰለ፡፡ ለዚህም ነው 11 እስላማዊ ፓርቲዎች በአንድ ተሰብስበው ለቅዳ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ለመጥራት የቆረጡት፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ግብጻውያን ምርጫ እንዲደርግ ይፈልጋሉ አሁን የሹራ ካውንስል ምርጫ፡፡ ስለሆነም አባይ ጥሩ የምርጫ ካርድ አይደለም ብላችሁ ታባላችሁ?

ሐ. የውክልና ጦርነት

እዚያ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ተጣራ

እዚህ ማዶ ሆኖ ክፉ ሰው ወይ አለው

ጎበዝ እንጠርጥር ይህ ነገር ለእኛ ነው፡፡ (ፋሲል ደሞዝ)

ሁለት የግብጽ ጄኔራሎች ወደ ሶማሊያ ሞቃዲሾ አምርተው ነበር በዚህ ሳምንት፡፡ የመሄዳቸው ዋና ዓላማም እንዳሉት የሶማሊያን ወታደራዊ ተቋማት እንደገና መልሶ ማቋቋም ነው ብለዋል የዜና ማሰረጫዎቹ፡፡ ነገር ግን የጦር ጥናት ሀ ሁን አስተማረ የሚባለው ቮን ክሎስዊትዝ “የሚመጣው/ነገ ትናንት/ያለፈው ነው” ይላል፡፡ ግብጾቹም ሆነ ኢትዮጵያ ለምን እንደሆነ ያውቁታል፡፡ ሶማሊያ የምታሳዝን ሀገር ናት፡፡ እዚህ ደረጃ የደረሰችው እና ብትንትኗ የወጣው አንድም ክፉ መሪ ጥሎባት ነው ዚያድ ባሬ የሚባል፡፡ ዋናው እና ተያያዡ ጉዳይ ግን ዚያድ ባሬን ልቡን ያሳበጡት የሳዳት እና የሙባርክ መንግስታት ናቸው ከግብጽ፡፡ ሶማሊያ ኢትዮጵያን ስትወርር በግብጽ ተባርካ እና ተዘክራ ነው፡፡ ከዚያድ ባሬ ውድቀት በኋላም አንዱን አንጃ ከአንዱ አንጃ እየለያየች ለእሷ ፈረስ የሚሆኑትን ብቻ ትሰበስብ የነበረችው ግብጽ ሶማሊያን መንግስት አልባ እንድትሆን ካደረጉ አገራት ቀዳሚዋ ናት፡፡ ምክንያቷም አንድ እና አንድ ነው የውክልና ጦርነት፡፡ ኢትዮጵያን በውክልና ጦርነት ለማዳከም ወይም የብሔራዊ ደህንነት ስጋት በመፍጠር ኢትዮጵያ ከልማት ይልቅ ብሯን እና ጊዜዋን በጦርነት እንድታሳልፍ ነበር የግብጽ እቅድ፡፡ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረትም ልብ ልብ የተሰማው ብግብጽ እና በመሰሎቿ ድጋፍ ነበር፡፡ ዳሩ ግን በአጭር ጉዞው መገታት ስለነበረበት ተመታ፡፡ ግብጽ እና አጋሮቿም አፈሩ፡፡ ታዲያ ይህች ዳርዳርታ በአዲስ መልክ ወደ ሶማሊያ ለመግባት የሚደረገው ሙከራ ግልጽ ነው፡፡ ሌላው ትልቁ ግልጽ ነገር ግን ሶማሊያ እና ሶማሊያውያን ጦርነት ሰልችቷቸዋል፡፡ የማንም የውክልና ጦርነት ማካሄጃነት ሰልችቷቸዋል፡፡ እናም ይህ የግብጽ ጉዞ ምኞት ነው፡፡ ኢትዮጵያን የማተራመስ ምኞት፡፡ በርግጥ ለሞሀመድ ሞርሲ ፓርቲ ሙስሊም ወንድማማቾች ህብረት ወንድም የሆነው የሰላፊያው ፓርቲ የአልኑር ፓርቲ (የብርሀን ፓርቲ ማለት ነው ነገር ግን ሰውየው እና ንግግሩ የፓርቲውም ዓላማ ጨለማ ነው፡፡) ተወካይ የቤተ ምንግስቱ ድራማ ላይ የሶማሊ ታጣቂዎችን እናስታጥቅ የኦነግንም እናስታጥቅ ነበር ያለው፡፡ እነዚህ ሽምቆች ደግሞ መውጫ መግቢያቸው በምስራቅ ነው፡፡

የማጠቀለየ መልዕክት

የኢትዮጵያ መልዕክት አንድ እና አንድ ነው፡፡ ሰላም፡፡ በአባይ ውሃ በፍትሐዊነት እና ምክንያታዊነት ሁሉም የአባይ ተፋሰስ ሀገራት በሉአላዊ መሬታቸው ያለ ማንኛውንም የተፈጥሮ ሀብት የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብት አላቸው፡፡ ወሰን ተሸጋሪ የሆኑትን የውሃ አካላት ኢትዮጵያ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንጠቀም ስትል ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ነው፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳ ግድብም የዚሁ አካል ነው፡፡ የፍትሐዊነት አካል፡፡ ስለዚህ ይህ ግድብ በምንም አይነት መልኩ የሚቆም አይደለም ለደቂቃዎች የሚስተጓጎል አይደለም፡፡ ግብጽ ከምንም በላይ የሚሻላት የኢትዮጵያ እጆች ለማቀፍ ተዘርግተዋልና መተቃቀፉ ነው፡፡ መተባበሩ ነው፡፡ ያ ሲሆን አባይ ለጋራ እድገት በጋራ ማልማት ይቻላል፡፡ ያ ካልሆነ እና ግብጽ እንዲህ መደንፋቷ ከቀጠለ እሱ ሌላ ነገር ነው፡፡ ኢትዮጵያ በጊዜውም ያለጊዜውም ሊዘንብ የሚችል ዝናብ ወይም ካፊያ መኖሩን ተገንዝባ ነገሮችን በጥንቃቄ ማየት እንዳለባት ካፊየውንም ዝናቡንም በአስተማማኝ መልኩ የሚከላከል ጥላ ማዘጋጀት እንዳለባት ታውቀዋለች፡፡ ለዚህም ነጋሪ አያስፈልጋትም፡፡ ለዛም ነው በልጇ በገነት ማስረሻ በኩል እንዲህ ስትል ያዜመችው…

በፍቅር ብንይዘው አባይ ያገር ዋርካ

ለዓለም ይበቃል እንኳን ለአፍሪካ፡፡

…………

ስንት ዘመን ቁጭት

ስንት ዘመን ፍጭት

ስንት ዓመት በጣሳ

ስንት አመት በወጭት

ፍሰስበት እና በሀገርህ ሜዳ

የሚቆጣን ካለ ያበጠው ይፈንዳ፡፡፡

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s