ኢትዮጵያና ግብፅ የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን የመፍትሄ ሀሳብን ለመተግበር ተስማሙ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትናንት ጀምሮ አዲስ አበባ  ላይ በውጭ  ጉዳይ  ሚኒስትሮች ደረጃ  ሲወያዩ  የነበሩት  ኢትዮጵያና  ግብፅ  ገድቡ በግብፅና በሱዳን ላይ  ሊኖረው የሚችለውን ተፅእኖ  እንዲገመግም የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ያስቀመጣቸውን  የመፍትሄ አሳቦች ለመተግበር ተስማምተዋል ።

ከውይይታቸው በኋላ  የኢፌዴሪ የውጭ  ጉዳይ ሚኒስትር  ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖምና  የግብፅ  አቻቸው መሃመድ ካመል አሚር በጋራ  በሰጡት  መግለጫ ፥ የባለሙያዎቹ ቡድን ባቀረበው የመፍትሄ  ሀሳብ መሰረት የግድቡን ኢኮኖሚያዊና  ማህበራዊ ተፅእኖዎች ለማወቅ  ተጨማሪ  ጥናት እንዲካሄድ አገራቱ ተስማምተዋል ።

አሁን  ሁለቱ አገራት በተስማሙት መሰረትም  ሱዳንን ባካተተ  መልኩ ተጨማሪ  ጥናቶችን  ማድረግንም ጨምሮ ሌሎች ባለሙያዎቹ  ያስቀመጧቸውን የመፍትሄ  ሀሳቦች ለመተግበር በአገራቱ የውጭ ጉዳይና  ውሃ  ሚኒስትሮች ደረጃ  ምክክሮችን ለማድረግ  ተስማምተዋል ።

የግብፁ የውጭ ጉዳይ  ሚኒስትር መሀመድ ከማል አሚር በመግለጫው ላይም  ሆነ ከዶክተር  ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር ባደረጉት  ውይይት  ላይ እንዳነሱት ፥ አገራቸው ታላቁ  የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በአገራቸው ላይ ተፅእኖ  ይኖረው ይሆናል  የሚል ስጋት  አለባት ።

የኢፊድሪ የውጭ  ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ  የግድብ ግንባታው የግብፅን  የውሃ  ስጋት  በቀረፈ መልኩ  እንደሚከናወን ማረጋገጫ መስጠቷን ጠቅሰው ፥ አባይን  በተመለከተ በፊትም  የያዘችው የጋራ  ተጠቃሚነት  የሚል አቋሟ  ዛሬም  እንደፀናና  ትብብርን  መሰረት  አድርጋ  ወደፊት  እንደምትገፋበት አረጋግጠዋል።

ሚኒስትሮቹ  በመጨረሻም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን  የበለጠ  ለማሳደግ ፥ በአሁኑ  ስብሰባቸው የተደረሱትን ስምምነቶች ተፈፃሚነትም ለመከታተል  ንግግራቸውን ለመቀጠል  ተስማምተናል ብለዋል ።

ኢትዮጵያ  ለታላቁ የህዳሴ ግድብ  ግንባታ  መቀላጠፍ የወንዙን ተፈጥሯዊ አቅጣጫ  ካስቀየረች በኋላ  በአንዳንድ የግብፅ  ፖለቲከኞችና ባለስልጣናት አፍራሽ  የሆኑና  የሁለቱን አገራት  ግንኙነት የሚጎዱ አስተያየቶች ሲሰጡ መቆየታቸው ይታወሳል።

በምንም  መልኩ የግድብ ግንባታዋን ለሰከንድ እንኳን እንደማታቆም የገለፀችው ኢትዮጵያ በፖለቲከኞቹና በባለስልጣናቱ አስተያየት ላይ ግብፅ  ማብራሪያ  እንድትሰጣት በይፋ ጠይቃም ነበር ።

ግብፅ ማብራሪያውን ለመስጠት  የውጭ  ጉዳይ  ሚኒስትሯ ወደ አዲስ አበባ  እንዲመጡ በጠየቀችው መሰረት መሃመድ ካመል አሚር በይፋ መልስ ለመስጠት ወደ መዲናችን መምጣታቸው ይታወቃል ።

በመግለጫው  ላይም  ስለ ጉዳዩ የተነሳላቸው የውጭ  ጉዳይ ሚኒስትሩ ትክክለኛውን የግብፅ ህዝብ ስሜትን ኢትዮጵያ  ታውቃለች ብለው ምላሽ መስጠት ጀመሩ ፤

ቀጥለውም በስሜት የተባሉት ሁሉ መባላቸውን እነዚህምን ሁሉ  ንግግሮች ወደኋላ  መተዋቸውና  አሁን አገራቸው በአባይ  ላይ  አብራ መስመጥን ሳይሆን መዋኘትን መምረጧን ገልጸዋል።

 FBC

በመቆያ ሃይለማርያም

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s