“ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች ድጋፍ ለአባይ (ኢፕሳ)” የሚል ተቋም ተመሰርተ

ከመላው ዓለም በተወጣጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሰኔ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. (22nd June 2013) በአባይ ጉዳይ ላይ ስብሰባ አደርጉ። ስለ ጉዳይ ቀድሞ በተዘጋጀ መነሻ ሃሳብ ባለሞያዎቹ ሰፊ ውይይት ካአደርጉ በኃላ “ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች  ድጋፍ ለአባይ” የተሰኘ በእንግሊዘኛው “International Ethiopian Professional Support for Abay (Nile)-IEPSA” ትኩረቱን በአባይ ወንዝ ላይ በሚሰሩ እና በታቀዱ ፕሮጀክቶች ያደረገ የባለሙያዎች የጥናት ተቋም አቋቋሙ፡፡

ይህ ተቋም በዋናነት በአሁኑ ወቅት ያሉትን ነባራዊ ሁኔታ ከተመለከተ በኃላ በዓለም ዙሪያ ያሉ ባለሞያዎች በየሞያቸው ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ተያያዥ በሆኑ በአባይ ላይ በሚሰሩ ቀጣይ የኃይል ማመንጫም ሆነ የመስኖ ግድብ ስራዎች ዙሪያ አስተዋጽኦ በተጠናከረና በተሰባሰበ መልኩ እንዲያደርጉ እና አገር ውስጥ ያለውን የሕዳሴ ግድብ ብሔራዊ የባለሞያዎች ቡድን በሙያ ለማገዝ በበጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን  የተቋቋመ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢፕሳ እንዲቋቋም ከአስገደዱ ምክንያቶች ዋና ዋናዎቹ አንደኛ ኢትዮጵያ እየሰራች ያለችው የሕዳሴው ግድብ እና በፕሮጀክቱ ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች በሰይንሳዊ ትንተና የተደገፈ መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች በተጠናከረ መልኩ ለዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ የሚያደረስ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም አለመኖሩ፤  ሁለተኛ የግብጽ ሕዝብ ፖለቲከኞች ከሚነግሩት መረጃ በስተቀር ኢትዮጵያ የምትገነባዎ ግድብ ለግብጽ እና ሱዳን ያለውን ጥቅም፣ ሌሎች ሀገሮች በአባይ ወንዝ ላይ ስላላቸው መብት እና ሌሎችም መረጃዎችን አለማግኘታቸው እና ይህም በራስጌ ሀገራት የውሃ ስራዎች በተለይ ኢትዮጵያ ላይ ያለቸው አመለካከት የተዛባ በመሆኑ፤ ሶስተኛ ኢትዮጵያዊያን በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ – ለምን ግድቡ አሁን ባለበት ቦታ ተሰራ? ለምን አንድ ግዙፍ ግድብ መስራት አስፈለገ? ሁለት ሶስት መካክለኛ ግድብ በተለያያ ቦታ መስራት አይቻልም ነበር ወይ? ከኤሌክትሪክ ሃይል ከማመንጨት በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከግድቡ ምን ትጠቀማለች? የሚሉ እና ተያያዥ ጥያቄዎች ማንሳታቸው እና ለዚህም የጠራ መለስ ስለሚያሻ ፤  አራተኛ በውጪ ዓለም ያለውን ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ በአንድ ላይ አምጥቶ የራሱን ሞያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የሚረዳ አካልም ሆነ የተመቻቸ ሁኔታ አለመኖሩ ናቸው፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ከፍተቶች በመነሳትም ኢፕሳ የተለያዩ ዓለማዎችን እና ግቦችን የቀረጸ ሲሆን በዋናነትም ከሁኔታው አንግባጋቢነት እና የተቀናጀ ስራ አስፈላጊነት አንጻር በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ በተለይ ለህዳሴ ግድብ ትኩረት በመስጠት ይንቀሳቀሳል፡፡ ስለሆነም ሳይንሳዊ ጥናትን መሰረት ያደረገ መረጃ ለሚመለከታቸው ክፎሎች ማድረስ፣ የህዳሴ ግድቡን ያጠናዊ አለም አቀፍ ኮሚቴ  ግድቡ በግርጌ አገሮች ላይ ያለውን አካባባዊ ተጽኖ ተጨማሪ ጥናት እና ሌሎችም ጉዳዮች ለህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ኮሚቴ ሙያዊ ድጋፍ እና ትብብር ማድረግ፣ የኢትዮጵያን ጥቅም ለማስጠበቅ በዓለምአቀፍ ደረጃ የህዝብ ግንኙነት ስራ እና የማግባባት ስራ መስራት፣ ስለ አባይ ወንዝ እና እንዲሁም ስለ ህዳሴ ግድብ የተሟላ የመረጃ ቋት ማዛጋጀት እና በወንዙም ሆነ በግድቡ ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚወጡ ሃሳቦችን ማየት፣ መተንተን፣ ካስፈለገ መልስ መስጠት  እና በውሃ አጠጠቃቀም ፣አከፋፈል እና ተዛማች ሞያዎች ዙሪያ ለኢትዮጵያዊያን ተማራማሪዎች የስኮላርሺፕ እድል ያፈላልጋል።

 

ኢፕሳን ያቋቋሙት ባለሙያዎች ከተለያየ የትምህርት እና የሙያ መስክ የተውጣጡ ሲሆን በዋናነትም ከአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ እና ካናዳ ዩኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ ፕሮፌሰሮች፣ ዶክተሮች እና የጥናት ባለሙያዎች፣ በተለያዩ ትልልቅ ኩባንያዎች የማሰሩ እና የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች እና የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ስብጥራቸውም በዋናነት ከተለያዩ ምህንድስና ሞያዎች፣ አካባቢ ሳይንስ እና አካባቢ ጥበቃ፣ ህግ፣ ምጣኔ-ሀብት፣ በውኃ እና በተሻጋሪ ወንዞች አስተዳደር፣ ዓለምአቀፍ ግንኙነት እና ኢንፎርሜሽን ቴክሎጅ ትምህርት ክፍሎች የተወጣጡ ናቸው፡፡

ዓላማዎቹንም ለማሳካት ኢፕሳ በዳይሬክተር የሚመራ ሲሆን በዋናነትም የምጣኔ ሐብት፣ ምህንድስና፣ አካባቢ ጥበቃና እርሻ፣ ህግ እና ዓለምአቀፍ ጉዳዮች፣ መረጃ እና የኢኒፎርሜሽን ቴክኖሎጅ፣ የህዝብ ግንኑነት እና የማግባባት  እና የወሰን ተሸጋሪ ወንዞች አስተዳድር ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡ ዳሬክተሩ፣ ጸሐፊው እና የየክፍሎች ሃላፊዎች በየስድስት ወሩ ይቀየራሉ። በቅርብም ተቋሙ ለተማራማሪዎች ጥሪ በማቅረብ በሎንደን በአባይ ወንዝ ላይ ታላቅ አውደ ጥናት ያካሄዳል።  ለዚህ ታሪካዊ ክስተት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለሙያ ሁሉ አባል በመሆን በተዋቀሩት ክፍሎች በመግባት የራሱን አስተዋጾዖ እንድታደርጉ እና እንድስተፉ ጥሪያችንን እንስተላልፋለ። በ abayipsa@gmail.com በሚለው ኢሜይል ሊያገኙን ይችላሉ።

 

ዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች  ድጋፍ ለአባይ (ኢፕሳ)

International Ethiopian Professional Support for Abay(IEPSA)

Email: abayipsa@gmail.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s