በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዋናው ግድብ የአርማታ ሙሌት ሥራ ተጀመረ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የተለያዩ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በሥራው ሂደት በርካታ የግንባታ ምዕራፎችንም አልፏል፡፡ የፕሮጀክቱ ዋንኛ አካላት የሆኑት የግድቡ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችና የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ሥራዎችም በመቀላጠፍ ላይ ናቸው፡፡

በፕሮጀክቱ ዲዛይን መሰረት ሲከናወኑ የነበሩት የተለያዩ የቁፋሮ ሥራዎች በመገባደድ ላይ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የዋናው ግድብ ግንባታ ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገረ እንደሆነ የፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ሥመኘው በቀለ ተናግረዋል፡፡

ኢንጅነር ሥመኘው እንደሚሉት አሁን በአብዘሃኛው የቁፋሮ ስራው እየተጠናቀቀ የአርማታ ሙሌት ሥራው ቀጥሏል፡፡ የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ግንባታ ለማከናወንም የወለል ቁፋሮ እየተጠናቀቀ ነው ብለዋል፡፡

ከዝቅተኛው ወለል የተጀመረው ይህ የአርማታ ሙሌት ሥራ 1 ሺህ 7 መቶ 80  ሜትር ርዝመትና 1 መቶ 45 ሜትር ቁመት ያለው ግድብ ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድረስ ይቀጥላል፡፡

የግድቡ ግንባታ እስኪያልቅ ድረስ ወንዙ በቋሚነት የሚፈስበት የብረት አሸንዳ ለመትከልም የመሰረት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ተግባር አስፈላጊ የሆኑ የግንባታ ሥራዎችም በመፋጠን ላይ ናቸው፡፡

የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ወንዙን ለመጥለፍ የሚያስችሉ መሳሪያዎች በማምረት ላይ ሲሆን ከጥቂት ቀናቶች በኋላ የተከላ ሥራውን እንደሚጀምር ነው የተገለጸው፡፡

በሁሉም የግንባታ ሥራዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት ፍተሻ እንደሚከናወን የገለጹት ኢንጅነር ስመኘው ፣ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅም 24 ሰዓት እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት ያሉት የሲቪልና የሃይድሮ መካኒካል ሥራዎችም በከፍተኛ ቅንጅት እየተከናወኑ ነው፡፡ ለግንባታው መቀላጠፍ አስፈላጊ የሆኑ 1 ሺህ 6 መቶ ማሽኖችን ጨምሮ ሁሉም ግብዓቶችና ቁሳቁሶች እንደተሟሉም ኢንጅነሩ ገልጸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ገ/ሚካኤል ገ/መድሕን

ምንጭ ኢሬቴድ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s