ጠ/ሚ ኃይለማርያም ሱዳን በህዳሴው ግድብ ላይ የወሰደችውን አቋም አደነቁ

  • Tuesday, 11 June 2013 17:07

 

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴግድብ ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ባቀረበው ሪፖርት ላይ ሱዳን የወሰደችውን አቋም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አደነቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ አህመድ ካርቲን በፅሕፈት ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ኢትዮጵያአጥኚቡድኑ ባጠናው ላይ የተሰጡትን አስተያየቶችን በማክበርእንደምትሰራ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ አህመድ ካርቲን በበኩላቸው አጥኚ ቡድኑ ያቀረበውን ሪፖርት የሶስቱንም ሀገሮች ጥቅም የሚያስከብር መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሱዳኖች መካከል ያለው ስምምነት የአፈፃፀም ችግሮችን ለመፍታት ኢትዮጵያ እገዛ እንድታደርግ ጠይቀዋል።

ሪፖርተር ፡- በቀለ ተመስገን

Ethiopia Radio and Television 

Leave a comment